የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ
የቢሮ ኃላፊ መልዕክት
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የክልሉን ወጣቶች ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንዲሁም የክልሉን ስፖርት እድገት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል። በአገር ግንባታ ሂደት ውስጥ ሰፊ የነቃና የተደራጀ ተሳትፎ ያለው፣ ብቁ ስፖርተኛና ጤናማ ማህበረሰብ ተፈጥሮ የማየት ታላቅ ራዕይ እውን ለማድረግ ባለፉት ዓመታት በስፖርትና በወጣቶች ዘርፍ ትልቅ ለውጥ ማምጣት ተችሏል። ስፖርት ለጤና፣ ለፍቅርና ለአንድነት ከሚያበረክተው ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ በተጨማሪ የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመፍጠር ሀገራዊ አንድነትን ለማስፈን ትልቅ ሚና አለው። ወጣቱን ትውልድ ለማነጽ፣ ታዳጊዎችን ለማብቃት፣ በስፖርታዊ እንቅስቃሴ ጤናማ ማህበረሰብ የመፍጠር ጉዞን ለማፋጠን የክልላችን ስፖርት በሳይንሳዊ መንገድ በመምራትና ዘመናዊውን የአስራር ስርዓት በመከተል በህብረተሰቡ ዘንድ የስፖርት ባህል እየሆነ ነው። በወጣቶች ስብዕና ልማት ማዕከላት የተከናወኑ መጠነ ሰፊ ስራዎች፣ የበጎ ፍቃድ ተግባራት፣ የአስተሳሰብ ስልጠናዎች የኢትዮጵያን የአንድነትና የብልጽግና ጉዞ ለማጠናከር በጉልህ የሚታዩ ውጤቶች መመዝገባቸውን ከዓይን የተሰወረ አይደለም።
ክልሉ የወጣቶችን ማህበራዊ፣ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የስፖርት ልማት ዘርፉን ለማገዝ በጥናትና ምርምር የጀመርነው ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል። የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ በሁሉም መዋቅሮች የተቀናጀ አሰራር በመዘርጋት ተቋማዊ ለውጥ ማምጣት ችለናል። ቢሮው ማህበራዊ መስተጋብርን ለማጠናከር በርካታ መልካም እድሎች ያላቸውን ስፖርቶች በመጠቀም የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ ለማጠናከር የወጣቱንና የስፖርት ቤተሰቡን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጀመሩትን ስራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጣለሁ። የሚከፋፍሉንን ነገሮች በማጥፋት ወንድማማችነታችንን በማጠናከር የስፓርታ ትንሳኤ እውን እንዲሆን በጋራ እንድንሰራ አደራ ማለት እፈልጋለሁ ። በሀገሪቱ በተጀመሩ የብልጽግና ተግባራት ላይ በንቃት እንድትሳተፉ እጋብዛችኋለሁ።