የወጣቶች ማካተት ንቅናቄና ተሳትፎ ዳይሬክቶሬት
የወጣቶችን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ማሳደግና ወጣቶች በተፈጠረላቸው የሥራ ዕድሎች በተለይም በጥቃቅንና አነስተኛ ዘርፎች ግንባር ቀደም ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ፣ በበጎፍቃድ ሥራዎች በንቃት እንዲሳተፉ፣ በየደረጃው ባሉ የወጣት ማህበራት ተሳታፊ በማድረግና ወጣቶች ሁለንተናዊ ስብእናቸው እንዲጎለብትና በተገነቡ ወጣት ስብዕና ማዕከላት ተጠቃሚ በማድረግ በአካል፤ በአዕምሮና በስነ-ልቦና የማጎልበት ስራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡መንግስትም የወጣቶችን ጉዳይ እንደ ዋና የልማት አጀንዳ በመያዝ የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ችግሮችን ለመፍታት ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
በዳይሬክቶሬቱ ስር ያለው አገልግሎት፡-
የንቅናቄና ግንዛቤ ፕሮግራሞች ማዘጋጀትና ማካሄድ
ወጣቶችን በተለያዩ ጉዳዩች ማሳተፍ
ወጣቶች በበጎ ፈቃድ አገልግሎት እንዲሳተፉ ማድረግ
የወጣት ማህበራት እንዲደራጁና እንዲጠናከሩ ማድረግ
ድጋፍና ክትትል ማካሄድ