የስፖርት ተሳትፎ እና ውድድር ዳይሬክቶሬት
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት፣ ለስፖርት ዘርፍ በተሰጠው ትኩረት ባለፉት ዓመታት በክልሉ የስፖርት ልማትን በተሻለ እና ወደ ለቀ ደረጃ ለመድረስ የሀገር አቀፍ የስፖረት ፖሊስን መሠረት በማድረግ እና በክልሉ በሁሉም መስክ ብቁ ንቁና በስነ-ምግባር የታነፀ፣ ተወዳዳሪ እና አሸናፊ ስፖርተኞችን ለማፍራት በልዩ ትኩረት እየተሰራ ይገኛል። በበርካታ ሀገራዊ እና ክልላዊ ውድድሮች በማዘጋጀትና ስፖርተኞችን በመሳተፍ፣ ለክልላችን ከፍተኛ ቁጥር ያለውን ሜዳሊያ ማስመዝገብ፣ ተችሏል። በመሆኑም፤ በርካታ ወጣቶች፣ ክልላችንን ወክለው በተለያዩ ስፖርት ዓይነቶች፣ የሀገራችንን ባንድራ፣ በዓለም አደባባይ ከፍ ማድረግ የቻሉ ስፖርተኞችን ማስመረጥ ተችሏል።
በዳይሬክቶሬት ስር ያለው አገልግሎት፡-
የስፖርት ኩነት እና ውድድር ፕሮግራሞች ማካሄድ
የስፖርት እውቅና እና ሽልማት ስርዓትን ማከናወን
የስፖርት ድርጅቶችና ባለሀብቱ በስፖርት ልማት ላይ እንዲሳተፉ ምቹ ሁኔታ መፍጠር