የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሥልጣንና ተግባር
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ስራ አስፈፃሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 195/2015 መሠረት ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-
የወጣቶች መብትና ጥቅም በማስከበር ዙሪያ ግንዛበና ንቅናቄ እንድፈጠር ያደርጋል
የወጣቶችን ሁኔታ የሚያመላክቱ ዝርዝር መረጃዎችን ይሰበስባል ያደራጃል በሚመለከታቸው ሁሉ እንዲታወቅ ያደርጋል፣
ወጣቶች በክልሉ የኢኮኖሚና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ለመሳተፍና ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችላቸው እድሎች የተመቻቸላቸው መሆኑን ያረጋግጣል፣
ወጣቶች እንደ ፍላጎታቸው ተደራጅተው ለመብቶቻቸው እንድታገሉና ችግሮቻቸውን ማስወገድ እንዲችሉ ያበረታታል ሁኔታዎችን ያመቻቻል፣
ወጣቶች በልማት፣ መልካም አስተዳደርና ዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ላይ ንቁ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ስልት ይቀይሳል ድጋፍ ይሰጣል፣
የወጣቶች አደረጃጀቶችን አቅም ለማጎልበት የሚያስችሉ ጥናቶችን ያካህዳል፣ ስልጠናዎችን ይሰጣል፣ የስልጠና አገልግሎት የሚሰጥበትን አሰራር ያመቻቻል፣ ያስተባብራል፣
በክልላችን የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን ተግባራትን ያስተባብራል፣ ይመራል ፣ጥናት ያደርጋል በመላው ህዝባችን ዘንድ ባህል ሆኖ እንዲወጣ ጥረት ያደርጋል፤
ወጣቶች በስነምግባር የታነጹና አውንታዊ አመለካከት እንዲያጎለብቱ የስብዕና ግንባታ ስራዎች ይሰራል፣ያስተባብራል አሉታዊና መጤ ባህሎች እንዲጠበቁ ይሰራል፣
ወጣቶች ማዕከላትን በማስፋፋት ወጣቶች ተገቢውን መረጃ እንዲያገኙ እምቅ ችሎታቸውንና ዝንባለያቸውን እንዲያወጡበት ድጋፍ ያደርጋል፣ ይከታተላል፣ ያስተባብራል፣
በክልሉ ለሚንቀሳቀሱ ስፖርት ማህበራት ፈቃድ ይሰጣል፣ ይሰርዛል፣ ፕሮግራማቸውን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፣
የስፖርት ውድድሮች እንዲዘጋጅ ያደርጋል ያስተባብራል፣
በክልሉ ስፖርት ማህበራት መካከል የሚነሱ ክርክሮችን በስፖርት ምክርቤት እንዲዳኝ ያደርጋል፣
የባህል ስፖርት እንዲታወቅና እንዲዘወተር ያደርጋል፣
የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እንዲዘጋጁ ያደርጋል የቴክኒክ ድጋፍ ይሰጣል፣
የስፖርት ትምህርትና ስልጠና እንዲስፋፋ ያደርጋል፣
በግል ለሚቋቋሙ የስፖርት ስልጠና ማዕከላት ፈቃድ ይሰጣል፣ ይመዘግባል፣ ይሰርዛል፣
ለስፖርት ልማት ዕድገት የሚሆን የገቢ ምንጭ እንዲፈጠር የተለያዩ ስልቶችን ይቀይሳል፣
ክልላዊ የውድድርና የስፖርት ማህበራት ደንብና መስፈርት ያዘጋጃል፣
የስፖርት ጉዳይን በሚመለከት መንግሥታዊና መንግሥታዊ ካልሆኑ አካላት ጋር የሚደረጉ ግንኙነቶችን ያስተባብራል፣
ዓላማውን ለማስፈፀም የሚረዱ ሌሎች ተግባሮችን ያከናውናል፡፡