Skip to main content
youthnews13

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)ለሀላባ ከተማ እግር ኳስ ቡድን አባላት በቤተ መንግስት አቀባበል እያደረጉላቸው ነው። (ዱራሜ፣ ግንቦት 4/2018 ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ለሀላባ ከተማ እግር ኳስ ቡድን አባላት በቤተ መንግስት አቀባበል አድርገውላቸዋል። 

በ2018 የውድድር ዘመን የከፍተኛ ሊጉ አሸናፊ በመሆን ወደ 2019 የሲቢኢ (CBE) ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊነቱን ያረጋገጠው የሀላባ ከተማ እግር ኳስ ቡድን ያገኘውን ድል ምክንያት በማድረግ ነው ዛሬ በቤተ መንግስት የምስጋና እና የእውቅና መርሐ ግብር እየተካሔደ ነው። በመርሐ ግብሩ የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር) በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክላስተር አስተባባሪዎች፣የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሃላፊ አቶ ጌታቸው ሌልሾ እና የሀላባ ዞን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።