AdminYouthsport
ሀገር አቀፍ ደረጃ በባህልና ስፖርት ሚንስቴር አዘጋጅናት በሀረር ክልል አስተናጋጅነት በሚካሄደው ባህላዊ ስፖርት ውድድሮችና ፌስትቫል የሚሳተፈው የማዕካለዊ ኢትዮጵያ ክልል የባህል ስፖርት ልዑክ ቡድን በከምባታ ዞን ዱራሜ ከተማ ቅድመ-ዝግጀት እያደረገ ይገኛል። (ዱራሜ፣ መጋቢት 16/2018 ዓ/ም) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የባህል ስፖርት ልኡካን ቡድን ጠንካራ የሆነ ቅድመ ዝግጅት እያደረገ ሲሆን ዛሬ በዱራሜ ሁለገቢ ስታዲየም እያተደረገ ያለውን ቅድመ ዝግጅት ም/በሮ ሀላፊና ስፖርት ዘርፍ ኃለፊ አቶ ሰይፉ አለሙ በአካል በመገኘት አበረታትተዋሉ ፡፡ የቅድመ ዝግጅት ስራዎቹ ዛሬም ከሰዓት በሁዋላ በተለያዩ ቦታዎች ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡